Skip to contentSkip to footer

ለዲሲ ምክር ቤት ወረዳ 4 የዲሞክራት ፓርቲ ዕጩ

የዲሞክራቲክ ፓርቲ ዋና ምርጫ በ ጁን 2፤ 2020 ይካሄዳል

እኔ የምታገለው ለባለሃብቶች ሳይሆን — ወረዳ 4 ውስጥ ላሉ ቤተሰቦች ነው

እኔ ያደኩት ወረዳ 4 ውስጥ ሲሆን ከተማው በመቀየሩ ምን ያህል እየተቸገርን መሆኑን እኔ እራሴ እየታዘብኩ ነው፤ ትምህርቴንም የተማርኩት ዲሲ ውስጥ ባለ የሕዝብ ትምህርት ቤት እና ሃዋርድ የሕግ ትምህርት ቤት ውስጥ ሲሆን፤ ሥሰራ እና ስታገል የኖርኩትም የዲሲ ረዳት ዓቃቢ ሕግ፤ የዲሞክራት ፓርቲ አክትቪስት እና የሕዝብ አገልጋይ ሆኜ ነው፡፡

የከተማችን አስተዳደር ውስጥ ያለውን ሙስና ለማስወገድ ስል ነው ቆርጬ የተነሳሁት፤ የወረዳ 4 የመጀመሪያዋ የፍታሃዊ ምርጫ እጩ ነኝ፤ ከንግድ ድርጅቶች አንድ ዶላርም ቢሆን አልቀበልም፤ ሠርተው ለሚኖሩ ቤተሰቦች ድምጽ ለመሆን ስል ነው በዚህ መልክ እየተወዳደርኩ ያለሁት፡፡

የምታገለው ከተማችን በእኩልነት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ነው ፤ የምንሮንበት ቤት፤ ልጆቻችን የሚማሩበት ትምህርት ቤት፤ ደህንነታችን፤ አዛውንቶች የሚያገኙት ግልጋሎቶች፤ እና ሌሎቹ ጉዳዮች ሁሉ የተሳሰሩ ናቸው፤ ለነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ደፋር እና ራዕይ ያለው በሕዝብ ንቅናቄ የተደገፈ አመራር እንዲኖር የግድ ይላል፤ ወረዳ 4 የመሪነቱን ደረጃ መያዣው ጊዜው አሁን ነው፡፡

ከተማችን እየበለጸገ ወደፊት በሚገሰግስበት ወቅት ወደኋላ ለቀሩት እጅ የመዘርጋት ሃላፊነት አለብን፡፡

የጃኔስ ራዕይ ለወረዳ 4 ነዋሪዎች ሁሉ የሚሰራ ነው፡፡

መኖሪያ ቤቶች፤ ሠርተው ለሚተዳደሩ ቤተሰቦች ወረዳ 4 ውስጥ መቆየት አስቸጋሪ እየሆነ ነው፤ አቅም የሚፈቅድ ቤቶች ላይ መዋለ ንዋይ ይፈስ ዘንድ፤ ቤት ለሚገዙ የሚደረገው እርዳት ከፍ እንዲል፤ የደሞዝ ጭማሪ እንዲኖር፤ እና የኪራይ ቁጥጥር እንዲጠብቅ እታገላለሁ፡፡

ትምህርት፤ የምታገለው እያንዳንዱ ልጅ ከሕዝብ ት/ቤቶች ጥሩ እና ውጤታማ ትምህርት የማግኘት እድል እንዲኖረው፤ ቅድመ ትምህርት ይስፋፋ ዘንድ፤ ወረዳ 4 ውስጥ ላሉ ትምህርት ቤቶች ሙሉ ባጀት እንዲመደብ እና አስተማሪዎች ከኛ ጋር ይቆዩ ዘንድ የሚያስፈልጋቸው ድጋፍ እና ክብር እንዲያገኙ ነው፡፡

የሕዝብ ደህንነት፤ ዲሲ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ “ወንጀል ላይ ጠንካራ እርምጃ” የሚል አመለካከት ላይ መመርኮዝ ጀምራል፤ ቢሆንም ግን ወንጀል አልቀነሰም፤ ጤናኛ የሕዝብ አመለካከት ላይ የተመረኮዘ በመረጃ የታቀፈ እርምጃ መውሰድ መጀመራችን ጊዜው አሁን ነው፤ ኒር (NEAR Act) ድንጋጌ ሥራ ላይ መዋል አለበት ብዬ አምናለሁ፤ በየመንገዱ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች ለመቅረፍ የተነደፉት ፕሮግራሞች እንዲስፋፉ እና ወንጀል የሚፈጸምባቸውን መሳሪያዎችን ከመንገድ ላይ እንዲወገዱ፡፡

ጤና፤ ዲሲ ውስጥ ጥቁር ሴቶች በወሊድ ጊዜ የመሞት እድላቸው ከማንኛቸውም የአገሪቷ ግዛቶች ጋር ሲነጻጸር መጠኑ ከፍ ያለ ነው፤ እንደዚህም ሆኖ ሐኪም ቤቶቻችን እየተዘጉ ነው፤ የወረዳ 4 ቤተሰቦች የሚያስፈልጋቸው የሕክምና ግልጋሎት ያገኙ ዘንድ ሐኪም ቤቶች ለታካሚዎች ምቹ መሆናቸው እና የጤና ተንከባካቢ ሠራተኞች መከበራቸው እንዲረጋገጥ እታገላለሁ፡፡

ተጠያቂነት፤ እነዚህን እና ሌሎች ችግሮቻችንን ለመቅረፍ፤ የከተማችን መሪዎች ከትርፍ በፊት ሕዝቡን ማስቀደም ይኖርባቸዋል፡፡

እኔ የምወዳደረው ወረዳ 4 ሁሉንም የሚያካትት እና በዕኩልነት የሚያስተናግድ ለሕዝብ ከሚቀርቡት ግልጋሎቶች አንስቶ እስከ ፓሊሲዎች ድረስ እንዲኖረው ነው፤ እርስዎ የዚህ አካል እንዲሆኑ እንሻለን፡፡

ደጋፊ፤

Join Us

Ward 4 can lead the way in making DC a place that works for all of us, not just a wealthy or well-connected few. We’re working to elect bold, new leadership ready to make it happen. Sign up to join the movement:

Donate

Janeese is fighting for a DC that works for you, not big donors. We are refusing corporate contributions and only taking donations up to $50. If you’re a DC resident, your donation will be matched 5 to 1 by DC’s new public financing program.

I'm Janeese Lewis George and I'm running for DC Council Ward 4